በስነ-ትምህርት ክህሎትና ውጤታማነት ላይ አጭር ስልጠናና ልምድ ማካፈል በኢንዳስትሪ ህይወት ቃል አ/ቤ/ያን ለሚያመልኩ ተማሪዎች መስጠት ተችሏል:: በቤተክርስቲያንቱ ወጣቶች ዘርፍ አገልጋዮች ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ስልጠና በግምቦት 24/ 2017 ዓ. ም እሁድ ከሰዓት ቦሃላ ከ1ኛ ደረጃ - መሰናዶ ትምህርት ቤት ለሚማሩ ተማሪዎች በስነ ትምህርት ክህሎትና ዉጤታማነት በሚል ርዕስ ስልጠና እና ልምድ ማካፈል መርሃ ግብር ተደርጏል:: የቤ/ቱ መጋቢ ፓስተር መርክነህ ሶርሳ እና የወጣቶች ዘርፍ አገልጋይ ዶ/ር ሄኖክ ዮናታን እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት ፕሮግራሙን በፀሎት ከከፈቱ በኋላ የልምድ ማካፈል ስልጠናውን ያቀረቡት ዶክተር ማቴዎስ አግዜ የወላይታ ሶዶ ዩንቨርስቲ ባዮሎጂ ትምህርት ክፍል አስተማሪ እና ተመራማሪ እና መ/ር ዳዊት ኡታ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የኮምፒውተር ሳይንስ መምህርና ተመራማሪ እንድሁም የሳይትክስ ኮምፒውተር ማሰልጠኛ ማዕከል መስራች በጋራ በመሆን ነው፡፡ የስልጠና ዋና ዓላማ የስነ ትምህርት ክህሎትና የትምህርት ውጤታማነትን የሚጎዱ ተግባራት እንዲገነዘቡት የሚያግዝ ነው፡፡ የስልጠናው ዋና ዋና ክፍልች የአነስተኛ ውጤት ምክንያቶች ፤ውጤታማ መማር እና አጠናን ዜደዎች፣የፈተና አሰራር ክህሎት ፤ቴክኖሎጂን ለትምህርት መጠቀም በሚለው ርዕሶች ላይ ያተኮረ ነው፡፡
በመጨረሻም ከሰልጣኞችና ከቤ/ያንቱ መሪዎች ስለስልጠናው መልካም ተጽእኖ ፈጣርነት እና በተላይ በዚህ ወቅት እጅግ በጣም አስፈላጊና መነቃቃት የሚፈጥር መሆኑን ገልጸው አሰልጣኞችን ባርከው ስያበቁ አሰልጣኞችም መሰል ስልጠናዎችን በተለያዩ ተቋማትም እንድምሰጡ ገልጸዋል:: ዘገባው የሳይትክስ መረጃና ማህደር ክፍል፡፡
ግምቦት 27፣ 2017 ዓ.ም.
ወላይታ ሶዶ