እንኳን ደስ አላችሁ ውድ ሰልጣኞቻችን! ከተሰማራችሁበት ስራና ትምህርት ጎንለጎን ትርፍ ሰዓታችሁን በመጠቀም በሳይትክስ ኮምፒዩተር ስልጠና ማዕከል ለሶስት ወራት መሰረታዊ የኮምፒውተር ክህሎት ስልጠና ተከታትላችሁ ስላጠናቀቃችሁ እንኳን ደስ አላችሁ አለን ለማለት እወዳለሁ:: በሩጫ መዳ ላይ ብዙ ሰው ይሰለፋል እስከ ፍጻሜ የሚደርሰው ሰው ግን ውስን ነው እንዲሁም የጀመራችሁትን የጥቂት ወራት ጉዞ በወኔና በቁርጠኝነት ለማጠናቀቅ መቻላችሁ በወደ ፊት ህይወታችሁም ላይ የሚትጀምሩትን የትኛውንም የህይወት እንቅስቃሴ በድል መጭረስ እንደምትችሉ ይህ ትልቅ ማሳያ ነው:: በአሁኑ በዲጂታል ዘመን ራሳችሁን ለመቀየር በተሰማራችሁበት ቦታ ውጤታማና ተወዳዳሪ ዜጋ ለመሆን የዲጂታል ኮምፒውተር ክህሎት ምርጫ የለለው ጉዳይ ስለሆነ የሸመታችሁትን እውቀትንና ክህሎትን በሚታገኙት አጋጣሚ ሁሉ ወደ ተግባር በማስገባት ልህቀታችሁን እንድታስቀጥሉ ላሳስባችሁ እወዳለው::በመጨረሻ የስልጠና ማዕከላችን ምርጥ አምባሳደር በመሆን ለሌሎችም በማጋራት የተለመደውን አብሮነታችሁን እንድትገልጹ በአክብሮት እየጠየኩ ለምትፈልጉት ለማንኛው ዓይነት ድጋፍና ትብብር ሁሌም ቢሮአችን ክፍት መሆኑን ለመግለፅ እወዳለሁ:: ሳይትክስ መስራችና ዋና አሳልጣኝ
መ/ር ዳዊት ኡታ
ግምቦት 30,2017 ዓም